የዶ/ር ጌታቸው ኃይሌ መታሰቢያ
ከሁሉ አስቀድሞ ዶ/ር ጌታቸው ኃይሌን የመሰለ አኩሪ ኢትዮጵያዊ ለሰጠን አምላክ ታላቅ ክብርና ምስጋና አቀርባለሁ። ዶ/ር ጌታቸው እጅግ በጣም የማከብረውና የምወደው ወዳጄ ነበር። ዶ/ር ጌታቸው የአገር ቅርስ ነው። ለአገሩ ብዙ ተመራምሯል፣ጽፏል ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፉ ትሩፋቶችን አበርክቷል። ግን ኢትዮጵያን የሚመጥናትን እንድታገኝ የተመኘላትን ሳትሆን ማለፉ ያሳዝነኛል።
ዶ/ር ጌታቸውና እኔ ከተዋወቅን ብዙ ዘመናችን ነው። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ገጠመኞቼን በዶክተር ጌታቸው ቋንቋ ፟“አንዳፍታ ላውጋችሁ።”
ሁለታችንም social activist ስለነበርን አንዳንድ ያዘጋጀሁትን መጣጥፍ ረቂቅ ስልክለት ሳይውል ሳያድር ሂሳዊ ምክሩን ወዲያው ይለግሰኝ ነበር።
ደግሞም ዶ/ር ጌታቸው የኔ የአማርኛ walking dictionary and encyclopedia ነበር። አንዳንድ የአማርኛ ቃላት ትርጉም ይቸግረኝና ስጠይቀው ያ እንደዛ ሥራ የሚበዛበት ሰው ጊዜውን ሳይቆጥብ በደንብ ያብራራልኝ፣ ያስረዳኝ፣ያስተምራኝ ነበር።
መጽሐፌን በእንግሊዝኛ በአጭር ጊዜ ለመጻፍ በአንድ ቴክኖሎጂ እኔ ስናገር እሱ የሚጽፍልኝ ብሞክር አልሆንልህ ብሎኝ አስቸገረኝ ብዬ እነግረዋለሁ። ዶ/ር ጌታቸው ታይፕ ማድረግ አትችልም ወይ ብሎ ይጠይቀኛል። እችላለሁ ግን እንደቴክኖሎጂው አያፈጥነኝም ስለው “ሰነፍ” አለኝ። በዛው ግሰጻ ታይፕ ማድረግ ጀምሬ መጽሐፌን ለማሳተም በቃሁ።
በእንግሊዝኛ የጻፍሁትን መጽሐፍ ወደ አማርኛ ለመተርጎም Value Engineering የሚለውን ቃል በአማርኛ ምን ልበለው ስለው “የፋይዳ ህንደሳ” በለው አለኝ። በአማርኛ መዝገበ-ቃላት ላይ ህንደሳ የሚለውን ቃል አለገኘሁትም ብለው “አቶ አባተ ደራሲው አኮ አንተ ነህ፣አንተ መጽሐፍ ላይ ከጻፍከው አንባቢው ይቀበለዋል፣ ቋንቋ እንደዛ ነው እኮ እየዳበረ የሚሄደው” አለኝ።
ዶ/ር ጌታቸው ኃይሌ እኔ የእግር ኳስ ጨዋታ አፍቃሪዎች ነበርን። በWorld Cup ወቅት ይደውልና ኳስ ጨዋታ እያየህ ነው እንዴ ይለኝ ነበር። አሁንም በ Euro 2021 ትዝታዬ እሱው ዶ/ር ጌታቸው ነበር።
ዛሬ የዶ/ር ጌታቸውን ሕይወት celebrate የምናደርግበት ዕለት ስለሆነ፣ ከእርሱ ትሩፋቶች አንዱን ለማስታወስ ሁላችሁም እንድታነቡት እሱ “ክተትን” ሲያቋቁም በእንግሊዝኛ የጻፍሁትን የድጋፍ መልዕክቴን፣ የክተት ጥሪው አሁንም ወቅታዊ ስለሆነ ከዚህ በታች እቅርቤዋለሁ።
እንግዲህ ያቺ ሁላችንም የማንቀርባት ዕለት ደረሰች። ወንድማችን ተለየን። ለውድ ባለቤቱ ለወይዘሮ ምሥራቅ እና ለልጆቹ፣ ለልጅ ልጆቻቸው፣ለመላው ቤተሰቡ ከልቤ የተሰማኝን ሀዘን እየገለጽሁ ለሁሉም መጽናናትን እመኛለሁ። የዶ/ር ጌታቸውን ነፍስ አምላካችን በገነት ያኑርልን። አሜን።
Commenti